መንፈሳዊ ጉባኤ

የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ለሦስት ቀን በስቶክሆልም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቀቀ።
የጉባኤውን ትምህርት ለመከታተል ከታች ያስቀመጥነውን ምስል ይጫኑ።

             abatachen siyastemiru

የመድኃኔዓለም አመታዊ በዓል


የጥቅምት መድኃኔዓለም አመታዊ በዓል ለሦስት ቀን በተዘጋጀ መንፈሳዊ ጉባኤ ሲካሄድ ቆይቶ ለዚህም በዓል ምዕመናን ከጉተንበርግ እና እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዋች በመምጣትና በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በአንድ ላይ በመገኘት ታቦተ ህጉ ወጥቶ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።

በዓሉ ምን ይመስል እንደነበር ለማየት ከስር ያሰቀመጥነውን የምስልና የቪድዮ ሊንክ በመጫን ይመልከቱ።

yewedefit zemari    abatachen siyastemiru

የተቀሩትን የጉባኤ ትምህርት ቪድዮ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

የቅዱስ መስቀል በዓል

እንኳን ለቅዱስ መስቀል በሰላም አደረሳችሁ። በየዓመቱ እንደምናደርገው ሁሉ ዘንድሮም የመስቀል ደመራ ከብረ በዓል በትላንታው እለት ይኽውም መስከረም አስራ ስድስት(16) ቀን ወይም በአውሮፓውያን አቆጣጠር ሰፕቴምበር ሃያ ሰባት(27) በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።

demera beal ቪድዮ         demera beal ፎቶግራፍ

የአስራ አራተኛው መንፈሳዊ ጉባኤ

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከሐምሌ 8 2003(ጁላይ 15 2011) ጀምሮ እስከ ሐምሌ 10 2003(ጁላይ 17 2011) ሲካሄድ የቆየው የአስራ አራተኛው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በአስደሳች ሁኔታ ተጠናቀቀ።
በብፁዕ አባታችን አባ ኤልያስ በአውሮፓ፣ በምሥራቅና ደብብ አፍሪቃ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተሰጥቶ ከተጀመረበት መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በተለያዩ የእግዚአብሔር ፀጋው በበዛላቸው መምህራን፣ ዘማሪያን እና መዘምራን ግሩም የሆነ መንፈሳዊ ትምህርት እና ዝማሬ በማቅረብ የጉባኤውን ታዳሚ ልዩ በሆነ መንፈሳዊ ስሜት ሲያወያይ ውልዋል።
ይህ በማናቸውም መልክ ልዩ የሆነ ከተለያየ ሃገር በመጡ ካህናት አባቶች እና ምዕመናን የተሳተፉበት ጉባኤ ምን ይመስል እንደነበር ለማየት ከታች ያስቀመጥነውን ሊንክ በመጫን ፎቶግራፎቹን ይመልከቱ።

ይህን ይጫኑ

የብፁዕ አባታችን አባታዊ ምክር