ከባንክ የተወሰደውን ዕዳ
በስዊድን ስቶክሆልም የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን ህንፃ ለመስራት ከባንክ የተወሰደውን ዕዳ በተደረገው መልካም እና በጎ ምግባር ርብርቦሽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ብድራችንን ከፍለን ለመጨረስ በቅተናል። ለዚህም ቅን እና በጎ ሥራ ያለምንም መሰልቸት በፀሎት፣ በጉልበት፣ በገንዘብ ሆነ በማናቸውም መንገድ ሁሉ እርዳታችሁ ሳይቋረጥ ለለገሳችሁን ሁሉ የልዑል እግዚአብሔር ፀጋ ይብዛላችሁ። የምስጋና ደብዳቤውን ያንበቡት
ቋንቋ ለማስተማር
በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚካሄድ የአማርኛ ትምህርት ለህፃናትና ለጎልማሶች ከመጋቢት አስር(10) 2003 ወይም በአውሮፓውያን አቆጣጠር Mars አስራ ዘጠኝ(19-2011)ዘወትር ቅዳሜ ከሰባት ሰዓት(13፡00)እስከ አስራ አንድ (17፡00)ሰዓት በሮግስቬድ(Rågesved Folkets Hus)ተጀምሮአል። የሚሰጡት የትምህርት አይነቶች፡ የአማርኛ ፊደል ማንበብና መጻፍ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖትን ታሪክና እና እምነት ማስተማር፣ የሃገራችንን ታሪክና ባህል ማሳወቅ። ይህንን እና ሌሎችም እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ በቅድመ ተከተል ይቀጥላል። ለለመመዝገብም ሆነ ለማንኛው ጥያቄ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ሊመጡ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 070-9522847 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የሰዓት ለውጥ
የሰዓት ለውጥን አስመልክቶ ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ ሁለት ሶስት ተኩል (8፡30)በበጋ የሚከናወነው የቅዳሴ ሥነ ስርዓት አሁን ከዚህ ሳምንት እሁድ ጀምሮ ይኽውም ከጥቅምት 19 (Oktober - 31) ወደ ክረምት ሰዓት ስለሚቀየር የቤተክርስቲያን የቅዳሴ ሰዓት ወደ ሶስት ሰዓት(9፡00)መለወጡን ቤተክርስቲያን ታሳስባለች።
