የሳምንቱ ምስባክ እና የሚዘመሩ መዝሙሮች

ቀን መዝሙር ምስባክ
2012-02-26
  1. እያለፈ ነው ዘመኔ
  2. እኔስ በምግባሬ
እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅድሱ

እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ ምስጋናና ውበት በፊቱ ቅዱስትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። መዝ. 95፦5

ለማውረድ እዚሀ ይጫኑ

2012-02-19
  1. እመቤቴ ማርያም እለምንሻለሁ
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐፅ እግዚአብሔር

ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ በረአድም ደስ ይበላችሁ ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጣ። መዝ. 2፦11

ለማውረድ እዚሀ ይጫኑ

2012-02-12
እግዚአብሔር ስቡሕ በምክረ ቅዱሳን ዐቢይ ወግሩም ዲቤኵሎሙ እለ ዐውዱ እግዚኦ አምላከ ኃያላን መኑ ከማከ

በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው አቤቱ የሠራዊት አምላክ እንደ አንተ ያለ ማን ነው። መዝ. 88፦7


2012-02-05
  1. ማርያም እላታለሁ
  2. ኃይሌን ጉልበቴን ታድሳለህ
በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ በሀገረ እግዚአ አያላን በሀገረ አምላክነ እግዚአብሔር ሣረራ ለዓለም

እንደሰማን እንዲሁ አየን በሠራዊት ጌታ ከተማ በአምላችን ከተማ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናናል። መዝ. 47፦8

ለማውረድ እዚሀ ይጫኑ

2012-01-29
  1. የሕይወት መሰላል
  2. ወደ ማደሪያው ገብቼ
እግዚአብሔር እግዚዕ አስተርአየ ለነ ግበሩ በዐለ በትሕፍሥት በኅበ ለአያሰትሐምምዎ እስከ አቅርቲሁ ለምሥዋዕ

እግዚአብሔር አምላክ ነው ለእኛም በራልን እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ የበዓሉንም መሥዋዕት በገመድ እሰሩት። መዝ. 117፦27

ለማውረድ እዚሀ ይጫኑ