1ኛ ሣምንት ዘወረደ

ወአልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ። ከሰማይ ከወረደው ክርስቶስ በስተቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። እስመ ዘእምላዕሉ መጽአ መልዕልተ ኩሉ ውእቱ። ከሰማይ የመጣው እርሱ ከሁሉ በላይ ነውና።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ......

2ኛ ሣምንት ቅድስት

ስያሜው ከላይ እንደገለጽነው የቅዱስ ያሬድ ሲሆን ቃሉ ግን የወጣው ወይም የተገኘው “ቀደሰ” አመሰገነ፣ለየ፣መረጠ፣አከበረ…… ከሚለው የግዕዝ አንቀፅ ነው። ስለዚህ “ቅድስት” የሚለው ቃል የሚቀፀለው ለሰንበት በመሆኑ ይህች ዕለት እና ከዚህች ዕለት ተነሥተን የምንቆጥራቸው ሰባት ዕለታት(አንድ ሣምንት) “ቅድስት” ተብሎ የጠራል።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ......

3ኛ ምኩራብ

ምኩራብ፦ ማለት ሰቀል መሰል አዳራሽ ማለት ነው። አይሁድ ስግደትና መሥዋዕት በኢየሩሳሌም ባለው መቅደስ ብቻ ነው ብለው ቢያምኑም (ዮሐ 4፥20) በየተበተኑበት ቦታ ምኩራብ እየሠሩ ትምህርተ ኦሪትን በመማር ሃይማኖታቸውን ያፀኑ ነበር።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ......

4ኛ መጻጉዕ

መጻጉዕ፦ ማለት በሽተኛ (ድውይ) ሕመም የፀናበት ማለት ነው። አራተኛው ሰንበት መጻጉዕ ተብሎ የተሰየመበት ምሥጢር በአራተኛ ክ/ዘመን በዘመነ ነገሥት በሽተኞችን በፈሳሽ ውሃ የማጥመቅ ሥርዓት በስፍት ይከናወን ስለነበረ ይህ ሣምንት (ሰንበት) መጻጉዕ ተባለ።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ......

5ኛ ደብረዘይት

ደብረዘይት፦ ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው።ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ካለው ከቄድሮስ ሸለቆ ራቅ ብሎ የሚገኝ ተራራ ሲሆን ዳግም የሚመጣበት ምልክት ለደቀ መዛሙርቱ በስፋት የገለጸበትና የማዳን ሥራውን ሲያጠናቅቅ ያረገበት ተራራ ነው።

በእግዚአብሔር ዘንድ የራስ ፀጉር ሣይቀር የተቆጠረ ነውና ሰው ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ መሬት በሞተ ሥጋ ምክንያት የተረከበችውን አፅምና ሥጋ አንዱንም ሣታጐድል አደራዋን የምትመልስበት ስለሆነ የሰው ልጅ ከሞት ሲነሣ በሕይወት የሠራውን ሥራ ይዞ ስለሚነሣ እና ሁሉም እንደየሥራው ዋጋ ስለሚከፈለው የጌታ አመጣጥ ለፍርድ ነው የተባለው ለዚህ ነው።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ......

6ኛ ገብር ኄር

ይህ ሰንበት (ሣምንት) ገብር ኄር ይባላል። ስያሜው እንደ ተለመደው የቅ/ያሬድ ነው። ስያሜውም የተወሰደው በማቴዎስ ወንጌል ም. 25 ከቁ. 14 – 31 ጌታ በሦስት አገልጋዮች ምሳሌ ካስተማረው ትምህርት ነው።

ከእነዚህ ሦስት አገልጋዮች መካከል ሁለቱ በመክሊቱ ምሳሌ በተሰጣቸው ፀጋ ወጥተው ወርደው ኃላፊነታቸውን የተወጡና የድካማቸው ዋጋ የሆነውን ትርፍ ከማግኘታቸውም በላይ በታማኘነታቸው ወደ ጌታቸው ደስታ የመግባት ዕድል ያገኙ ሲሆን ከሦስቱ አንደኛው ግን መክሊቱን ሲመልስ ጌታውን የሚያሳዝንና የማይገባ ቃል በመናገሩ ወደ ጨለማ ለመወርወር የበቃ ክፉ ባሪያ ነው።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ......

7ኛ ኒቆዶሞስ

”ምሥጢር” ተብሎ የተሰየመ መንፈሳዊ ትምህርት ሁሉ በሰው ሰውኛ ማለትም በሥጋዊ ትምህርት አንፃር ሲመለከቱት ከባድ ነው። ምክንያቱም በአይነ ሥጋ እየተመለከትነው በሚፈጸመው ሥርዓት የሚገኘውን ልጅነትና ክብር በዓይነ ሥጋ ማየት ስለማንችል ነው። ለምሣሌ ጥምቀት ሲፈጸም በዓይን ይታያል። ልጅነት ሲሰጥና መንፈስ ቅዱስ ሲያድርበት ግን አይታይም።

ለዚህም ነው ኒቆዲሞስ ”ሰው ሁለተኛ ካልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” ሲባል ወዲያውኑ መቀበል የቸገረው።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ......